ሳሙኤል ፍሬው በወንዶች 3000ሜ. መሰናክል ለዳይመንድ ሊጉ ፍፃሜ በሚያበቃው ደረጃ ላይ ይገኛል።
በ2026 ዓ.ም. ዋንዳ ዳይመንድ ሊግ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ለብራስልሱ ፍፃሜ ለመብቃት እየተደረገ ባለው የነጥብ ፉክክር ሶስት አትሌቶች ከወዲሁ ለፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ሞሮኳው ሱፊያን ኤል ባካሊ (24 ነጥብ) እንዲሁም ኬንያዊውያኑ ኤድሙንድ ሴረም (24 ነጥብ) እና ሲሞን ኮኤች (17 ነጥብ) በመያዝ ለብራስልሱ ፍፃሜ ማለፋቸውን ባረጋገጡበት በዚህ ርቀት ኢትዮጵያዊው ሳሙኤል ፍሬው (12 ነጥብ) በአምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በአጠቃላይ 10 አትሌቶች ለብራስልሱ የፍፃሜ ውድድር በሚያልፉበት የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ውድድር ሳሙኤል ፍሬው ሁለተኛ ሆኖ ባጠናቀቀበት የዶሀ ዳይመንድ ሊግ 7 ነጥብ፣ እና አራተኛ ሆኖ በጨረሰበት የፓሪስ ዳይንድ ሊግ 5 ነጥብ በማግኘት በአጠቃላይ በ12 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በዚህ ርቀት በቀሪው አንድ ውድድር ላይ በሚኖራቸው ተሳትፎ እና በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት ለብራልሱ ፍፃሜ የማለፍ ተስፋ ያላቸው ሁለቱ ኢትዮያውያን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ7 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ገመቹ ጎዳና እና በ6 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አብርሀም ስሜ ናቸው፡፡ ገመቹ ጎዳና የዳይመንድ ሊግ የመጀመሪያ ተሳትፎውን ባደረገበት የፓሪስ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል የግሉን ምርጥ 8፡05.55 ሰዓት በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆኖ መጨረሱ ይታወሳል፡፡ የፓሪ ዳይመንድ ሊግ ተሳትፎውም በዘንድሮ የውድድር ዓመት በርቀቱ ያደረገው ስድስተኛ ውድድሩ ነበር፡፡
በ2026 ዳይመንድ ሊግ የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ነጥብ የሚመዘገብበት የመጨረሻ ውድድር በሲሌሲያ (ፖላንድ) ዕሁድ ኦገስት 23-2026 የሚካሄድ ይሆናል።

Men’s 3000m steeplechase Diamond League Standings as of July 28, 2026.
Samuel Firewu is in a position to qualify for the Diamond League final in the men’s 3000m steeplechase.
In the race to qualify for the 2026 Wanda Diamond League final in Brussels for the men’s 3000m steeplechase, three athletes have already secured their spots. While Morocco’s Soufiane El Bakkali (24 points) and Kenyans Edmund Serem (24 points) and Simon Koech (17 points) have confirmed their qualification, Ethiopia’s Samuel Firewu (12 points) currently sits in fifth place.
With a total of ten athletes set to advance to the Brussels final, Samuel Firew holds fifth place with 12 points, accumulated from the 7 points earned by finishing second at the Doha Diamond League and the 5 points gained by finishing fourth at the Paris Diamond League.
The two Ethiopian athletes hoping to qualify for the Diamond League final in this event, based on their participation and results in the remaining race, are Gemechu Godana, currently ranked 11th with 7 points, and Abraham Seme, ranked 13th with 6 points. Gemechu Godana notably finished second in the men’s 3000m steeplechase at the Paris Diamond League, his debut in the series, clocking a personal best of 8:05.55. That race in Paris marked his sixth competition of the season in this event.
The final race for points in the men’s 3000m steeplechase for the 2026 Diamond League season will take place in Silesia, Poland, on Sunday, August 23, 2026.
